ጴጥሮስ ያቺን ሰዓት
ተላከ፤ ከአራዳ ልጆች
አቅራቢ፤ መስፍን ማሞ ተሰማ
ቀዳሚ፤ ይድረስ ለዲበኩሉ!
ወዳጃችን ዲበ! ለጤናህ እንደምን አለህልን? እንዲያው ለመሆኑ እንዲያው ለነገሩ፤ ምነው ድምፅህ ጠፋ ከቀዬው ካገሩ? ምነዋ ራቀን የደብዳቤህ ትሩፋቱ፤ የፈረንጅ ሀገር ሁሉ ወጉ? እዚህ በጦቢያችን እዚህ በቀያችን ወዳጅ ሲጠፋ፤ ድምፁ አልሰማ ሲል – ምነው የበላው ጅብ አልጮህ አለ? ይባል ነበር። እንግዲህ ነበር ነው። ድሮ።
ዛሬ ዘመንማ እንኳን ጅብ የሚኖርበት ጫካ እንኳን የሚመሽግበት ጎሬ ኖሮት ሰው ሊበላ ቀርቶ እኛም መኖሪያ አጥተናል፤ ወንድምአለም። እና ይኸውልህ ዛሬ ዘመን ወዳጅ ጓደኛ ዘመድ አዝማድ ድንገት ድምፁ እልም ድርግም ካለ፤ ሲጠሩት ካልሰማ፤ ሲፈልጉት ካልተገኘ – ወይ ቃሊቲ ወርዷል፤ ወይ ሰፈራ ተጭኗል፤ ወይ ‘በድንገተኛ አደጋ’ በመኪና አስገጭተው አልያም በዱርዬ አስደብድበው ተቀጥፏል፤ ካልሆነም ተሰዷል። … (ሙሉውን ጽሑፍ በPDF ያንብቡ!)