በጋምቤላ ሃያ የኮሌጅ ተማሪዎች በጥይት ተገደሉ

አምስቱ ክፉኛ ቆስለዋል

Ethiopia Zare (ረቡዕ የካቲት 5 ቀን 2004 ዓ.ም. March 14, 2012)፦ ከትናንት በስቲያ ሰኞ መጋቢት 3 ቀን 2004 ዓ.ም. ከቀኑ 10 ሰዓት አካባቢ ከጎደሬ ወደ ጋምቤላ በሚጓዝ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ላይ ተሳፍው የነበሩ 25 ወንዶች ተማሪዎችና ወጣቶች ካርሚ በምትባል ስፍራ ላይ በጥይት ተደብድበው 20ዎቹ ሲሞቱ 5ቱ ደግሞ ክፉኛ ቆስለዋል።