ብሔራዊ ባንክ የብርን የመመንዘር አቅም ዝቅ ሊያደረግ ነው
ባለፈው የካቲት ወር 2001 ዓ.ም የብር የምንዛሬ ምጣኔን በ22 በመቶ ዝቅ እንዲል መመሪያ አስተላልፎ የነበረው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በቅርቡም ተመሳሳይ እርምጃ ሊወስድ እንደሚችል ምንጮች ገለጹ፡፡ በአዲሱ የምንዛሬ ማስተካከያም በሕጋዊው የምንዛሬ ገበያ አንድ የአሜሪካን ዶላር በ14 ብር ሊመነዘር ይችላል፡፡ እንደምንጮች ገለጻ ከኾነ የዶላር እጥረቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ በመምጣቱ ምክንያት በመደበኛው እና በኢመደበኛው (Parallel Exchange Market) ገበያዎች መካከል ያለው የምንዛሬ ምጣኔ ልዩነት እየሰፋ ሄዷል፡፡ በሣምንቱ የምንዛሬ ገበያ አንድ ዶላር በመደበኛው ገበያ በአማካይ በ13.40 ብር የሚመነዘር ሲኾን በድብቅ በሚካሄደው ኢመደበኛ ገበያ ግን አስከ 14 ብር ድረስ ይመነዘራል፡፡ ይህም በሁለቱ የምንዛሬ ገበያዎች ያለውን ልዩነት (premium) እንዲሰፋ አድርጎታለ፡፡ በውጭ ምንዛሬ እጥረቱ ምክንያት ንግድ ባንኮች በወጪ እና ገቢ ንግድ የተሰማሩ ደንበኞቻቸውን በአግባቡ ማስተናገድ እየተሳናቸው እንደኾነም መረጃዎቹ ይገለጻሉ፡፡ ሙሉውን ጽሑፍ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ ወይም ወደ አማርኛው ክፍል ይሂዱ።