የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ አፅራረ ቤተ ክርስቲያንን ለመከላከል በሚያደረገው ጥረት ማንኛውንም ድጋፍ እንደሚሰጥ የአ/አበባ ሀ/ስብከት አስታወቀ


  • የፕሮቴስታንታዊ-ተሐድሶ-ኑፋቄ ጥመት – አሰግድ ሣህሉ እንደ ማሳያ (ከደብረ ይባቤ ቅዱስ ያሬድ ቤተ ክርስቲያን ሰንበት ት/ቤት ዘገባ የተገኘ)
 ቀንደኛ የተሐድሶ ኑፋቄ አቀንቃኝ የተባለው አሰግድ ሣህለ

(ደጀ ሰላም፤ ፌብሩዋሪ 10/2011፤  የካቲት 3/2003 ዓ.ም)፦ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ሐዋርያዊ ተልእኮ ለማፋጠን እና ለማስፋፋት፣ የተቋቋመበትን ዓላማ ለማሳካት፣ ኮሌጁንም ከማንኛውም አጽራረ ቤተ ክርስቲያን አካላት ለመጠበቅ በሚያደርገው ጥረት ሁሉ ድጋፍ የሚሰጥ መሆኑን አስታወቀ፡፡ የሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት ይህን ያስታወቀው፣ የኮሌጁ አስተዳደር ጉባኤ  የኮሌጁን የቅበላ መስፈርት ባለማሟላቱ ኅዳር 23 ቀን 2003 ዓ.ም ከትምህርት ገበታ ያገደው አሰግድ ሣህለ የተባለ ቀንደኛ የተሐድሶ ኑፋቄ አቀንቃኝ፣ ‹‹በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ውስጥ የቤተ ክርስቲያን አባል እንደሆነ የሚያቀርበው የመብት ጥያቄ ተቀባይነት የሌለውና በሀገረ ስብከታችን ውስጥ የቤተ ክርስቲያናችን አባል አለመሆኑን›› በመግለጽ ለኮሌጁ በጻፈው ደብዳቤ ነው፡፡

(Read More ወደሚቀጥለው ገጽ ይዞራል . . . . .)