የከተራ-ጥምቀት በዓል ቅድመ ዝግጅት በተጠናከረ ሁኔታ በመካሄድ ላይ ነው
- በመዲናይቱ አዲስ አበባ በ62 ማኅበራት የተደራጁ ከ25‚000 በላይ ወጣቶች በቅድመ ግጅቱ ታቦተ እግዚአብሔር የሚያልፋባቸውን ጎዳናዎች በማጽዳት እና በመደልደል፣ መንገዶችን እና አደባባዮችን በሰንደቅ ዓላማ በማሸብረቅ ግንባር ቀደም ተሳትፎ እያደረጉ ነው
- የማኅበራቱ አደረጃጀት እና ባለቤትነት በጠቅ/ቤተ ክህነቱ የስብከተ ወንጌል እና ሐዋርያዊ ተልእኮ መምሪያ እና የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ መካከል ውዝግብ ያስነሣ ሲሆን በቀጣይ ወጣቶቹን ‹‹የስብከተ ወንጌል እና ሐዋርያዊ ተልእኮ መምሪያው በትምህርተ ወንጌል አንጾ ለአገልግሎት በማዘጋጀት በሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ሥር እንዲዋቀሩ ስምምነት ተደርሷል፤›› ተብሏል፡፡ ማኅበራቱን ከክፍለ ከተሞች የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጉባኤ አመራሮች እና ከማኅበረ ቅዱሳን ጋራ ለማጋጨት የታቀደውን ተንኮል እንደደረሱበት የገለጹት የማኅበራቱ ተወካዮች በበኩላቸው ከብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያሪኩ ተሰጥቶናል በሚሉት ፈቃድ መሠረት በስብከተ ወንጌል እና ሐዋርያዊ ተልእኮ መምሪያ ሥር መቆየትን እንደሚመርጡ በመግለጽ ላይ ናቸው፡፡
(Read More ወደሚቀጥለው ገጽ ይዞራል . . . . .)
