በሐዋሳ ለብፁዕ አቡነ ገብርኤል ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው
- ከ20 በላይ መኪኖች እና ሰባት ሞተረኞች ጥቁር ውኃ ላይ ተሰልፈው ተቀብለዋቸዋል፤ ፓትርያርኩ አልተገኙም፡፡
- ብፁዕነታቸው፣ ‹‹ውበት የሚኖረው በአንድነት ውስጥ በመሆኑ በኅብረት አንድ ሆነን መገኘት ያስፈልገናል፤›› በማለት መክረዋል፡፡
- ጥቂት ቲፎዞዎች ጥቁር ጨርቅ ሲያውለበልቡ ታይተዋል
- እነ ያሬድ አደመ የተለቀቁት፣ ‹‹ዐቃቤ ሕግ የምርመራ ሂደቱን ከጊዜ ቀጠሮው በፊት ማጠናቀቁን ሪፖርት በማቅረቡ የዋስ መብት ተጠብቆላቸው ነው›› ተብሏል፡፡
(ደጀ ሰላም፤ ኖቬምበር 13/2010፤ ኀዳር 4/2003 ዓ.ም)፦ በጥቅምቱ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ የሲዳማ፣ አማሮ እና ቡርጂ ዞኖች እና ልዩ ወረዳዎች ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሆነው የተመደቡት ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ዛሬ ረፋድ ላይ ሐዋሳ ከተማ ሲገቡ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡ ሊቀ ጳጳሱን ለመቀበል ከሀገረ ስብከቱ፣ ከአጥቢያ አብያተ ክርስቲያን እና ከምእመናን ተውጣጥቶ የተቋቋመው 40 አባላት እና ልዩ ልዩ ዘርፎች ባሉት የአቀባበል ኮሚቴ፣ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ከብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል፣ ብፁዕ አቡነ ያሬድ እና ብፁዕ አቡነ ሚካኤል ጋራ በሐዋሳ ከተማ መግቢያ – ጥቁር ውኃ አምስት ሰዓት ግድም ሲደርሱ በበጎ ፈቃድ በተሰለፉ ከኻያ በላይ መኪኖች እና ሰባት ሞተር ሳይክሎች በማጀብ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡
(Read More ወደሚቀጥለው ገጽ ይዞራል . . . . .)
