ጠቅላይ ቤተ ክህነት በአስተዳደራዊና መዋቅራዊ ማሻሻያ ዋዜማ


(ደጀ ሰላም፤ ኦክቶበር 8/2010፤ መስከረም 28/2003 ዓ.ም):- ጠቅላይ ቤተ ክህነት አስተዳደራዊና መዋቅራዊ ማሻሻያ ሊደረግበት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የደጀ ሰላም ምንጮች አስታወቁ። 
ከትናንት በስቲያ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ም/ዋና ሥራ አስኪያጅ የነበሩት ንቡረ ዕድ ኤልያስ አብርሃ ከመስከረም 28/2003 ዓ.ም ጀምሮ ከሥልጣናቸው እንደሚነሡ መዘገባችንን መነሻ ያደረጉት ምንጮቻችን እንዳብራሩት ጉዳዩ ንቡረ ዕዱን የማንሣት ወይም የማዘዋወር ሳይሆን የኃላፊነት ሽግሽግ እንደሚሆን ገልጸዋል። ምንጮቹ የሚሉት ትክክል ከሆነ በቤተ ክህነቱ አስተዳደር ላይ ሁነኛ የአሠራር ለውጥ ይኖራል ተብሎ ይገመታል። ዝርዝሩን በቅርቡ እንደምንመለስበት እናስታውቃለን።