አዲስ የጡመራ መድረክ (ብሎግ) በቀሲስ ያሬድ ገ/መድኅን
(ደጀ ሰላም፤ ኦገስት 31/2010፤ ነሐሴ 25/2002 ዓ.ም)፦ ምእመናን ስለ ቤተ ክርስቲያናቸው ወቅታዊ ሁናቴ የሚያውቁባቸው አዳዲስ የጡመራ መድረኮች በየጊዜ እየተመለከትን ነው። ዲ/ን ዳንኤል ክብረት ላለፉት አራት ወራት ግሩም ግሩም ጽሑፎችን እና የመወያያ ነጥቦችን እያነሣ ሲሆን ሌላው ሰባኬ ወንጌል ቀሲስ ያሬድ ገ/መድኅንም በበኩላቸው የራሳቸውን መጦመሪያ (የጡመራ መድረክ http://www.kesisyaredgebremedhin.com/) ፈጥረዋል። ደስ የሚያሰኝ ነው። ባወጡት መርሐ ግብር እንዲዘልቁም እንመኝላቸዋለን። ማስታወቂያቸው እንደሚከተለው ይነበባል።
—————————————————————–
ከማክሰኞ ጳጉሜን 2 (September 7) ቀን ጀምሮ በየሳምንቱ ማክሰኞ ከእናንተ ለሚቀርቡ ጥያቄዎች መልስ ይሰጣል። ስለዚህም ክርስቲያናዊ ሕይወትን የተመለከቱ ጥያቄዎቻችሁን ወደ [email protected] መላክ የምትችሉ መሆኑን በአክብሮት እንገልጻለን። የያሬድ ቤት ጽሑፎችን እንደሚከተለው ያወጣል፦
ማክሰኞ
ጥያቄ አለኝ (የጥያቄዎቻችሁ መልሶች)
ዓርብ
ክርስትናና ወጣትነት
በተጨማሪ
ግጥሞችና ሌሎች ሥነ ጽሑፎች እንዳስፈላጊነቱ በተለያዩ ጊዜያት ይቀርባሉ።