የዘረኛው አምባገነኑ ወያኔ አገዛዝ ማናለብኝነትና ጀብደኝነት ከልክ ማለፉ ተገለጸ

ባሳለፍነው ሳምንት በሃገር ውስጥ እየታተመ ለንባብ የሚወጣው “ፍትሕ” ጋዜጣ ባወጣው ዘገባ ራስ ዳሽን ተራራ በአዲሱ የተማሪዎች መማርያ መጻሕፍት ትግራይ ክልል ውስጥ እንደሚገኝ ተደርጎ መጻፉን መግለጹን ተከትሎ በርካታ የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች ቁጪታቸውን እየገለጹ ነው፡፡

ፍትህ ጋዜጣ አቶ ያሬድ የተባሉ የመኢአድ አባልን ዋቢ በማድረግ ጎንደር እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ‹‹የትምክህተኞች መሠረት ናት›› በሚል ምንም አይነት ልማት ሳይካሄድባት በተጽእኖ ስር እንደነበረች ገልጾ በጎንደር የነበሩት እነ ዴፖ፣ መብራት ኀይል፣ የትራክተር መገጣጠሚያዎች እና የዉሃ ማጣርያዎች “ተመዝብረው ወደ ትግራይ ተወስደዋል” ማለቱ ይታወቃል፡፡

የራስ ዳሸን ተራራን ወደ ትግራይ ክልል የመካተቱን ጽሁፍ አስመልክቶ ዘጋቢያችን አስተያየት የጠየቃአቸው በርካታ የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች እንደገለጹት፣ ይህ ጽሁፍ ቀልድ መሆን አለበት፣ ለዘመናት በጎንደር ክልል ውስጥ መሆኑ የሚታወቀውንና እጂግ በርካታ ለሆኑ ቱሪስቶች መስህብ እንደሆነ የሚታወቅን ክልል ወደትግራይ መውስድ ማለት እውነትም የወያኔው አገዛዝ ከሚገባው በላይ ንቆናል ማለት ነው፣ ፣ ለማንኛውም ሂደቱን በንቃት እንከታተላለን ማለታቸውን ገልጾልናል::

ቀደም ብሎ “ከጎንደር ተቆርሶ ለሱዳን ይሰጥ የተባለውን መሬት የቀድሞው የአማራ ክልል ምክትል ፕሬዘዳንትና የአሁኑ ዋና ፕሬዘዳንት ደመቀ መኮነን በፊርማው ማጽደቁ ነገር ግን የቀድሞው የክልሉ ፕሬዝዳንት አቶ አያሌው ጎበዜ እና የጎንደር አስተዳዳሪ ጌታቸው ጀንበር አንፈርምም ብለው መቃወማቸው ይታወቃል፡፡

ይህን የወያኔ አምባገነን አገዛዝ መሰሪ አካሄድ የተገነዘቡ አንድ የጎንደር ነዋሪ እንደገለጹት ቀደም ብሎ ከጎንደር እስከ ጋምቤላ የሚደርሰውን ለም መሬት ለሱዳን አሳልፎ ለመስጠት በመስማማት ለሆዱ ያደረው ደመቀ መኮንን በፊርማው በማጽደቁ ለአከናወነው ተግባር የትምህርት ሚንስትር ሆኖ ተሾሞ እንደነበርና አሁንም አምባገነኑ አገዛዝ በአማራው ህዝብ ላይ የተለያዩ በደሎኦችን ለመፈጸም እንዲመቸው ደመቀ መኮነንን የክልሉ ፕሬዘዳንት በማድረጉ ይህ የራስ ዳሸንን ወደ ትግራይ ክልል የመውሰዱ ስራ ተግባራዊ የማይሆንበት ምክንያት እንደማይኖር ግምታቸውን ገልጸዋል::