የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን ድርጅት ወደ ኢትዮጵያ የሚካሄደውን ስርጭት እንደገና መጀመሩን አስታወቀ

ባለፈው አመት ተመስርቶ ስርጭቱን የጀመረው፤ ነገር ግን በወያኔ አገዛዝ በተደረገበት ተደጋጋሚ አፈና የሳተላይት ስርጭቱን ለማቆም የተገደደው የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን ድርጅት – ኢሳት – ወደ ኢትዮጵያ የሚያደርገውን ስርጭት እንደገና መጀመሩን አሳውቋል።

ኢሳት በአጭር ጊዜ ውስጥ በኢትዮጵያ ውስጥ ከፍተኛ ተወዳጅነትን ያተረፈ ሲሆን፤ በወያኔ አገዛዝ ቁንጮዎች ዘንድ ከፍተኛ ስጋትን ፈጥሮ እንደነበር መዘገባችን ይታወሳል።

ድርጅቱ ኅዳር 23 ቀን ባወጣው መግለጫ፤ ወደ አየር መመለሱ የበርካታ ወራት ጥረት ውጤት መሆኑን ጠቅሶ፣ ኢትዮጵያውያን በሚቻላቸው መንገድ ሁሉ እንዲረዱት ጥሪ አቅርቧል።

የአዲሱ ስርጭት መረጃ፦

Thaicom5 Satellite, C-Band at 78.5E, Transponder:6G, Downlink:3640H, Symbol:28066, FEC ¾