የወያኔው ገዢ ቡድን ሰሞኑን ነጋደዎችን እየከፋፈለ እና ለጥቃት እያዘጋጃቸውም መሆኑ ተዘገበ
ዘረኛው የወያኔ ገዢ ቡድን ከህዝቡ ገንዘብ ለመዘረፍ በማሰብ የለውጥ እቅድ በማለት ያወጣውን እቅድ ተግባራዊ ለማድረግ በሚል ስም አገኘዋለሁ ብሎ ያሰበውን ገንዘብ ማሰባሰብ የተሳነው መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን ሰሞኑን የነጋዴው ህብረተሰብ ላይ ጫናውን በማብዛትና የተለያየ ተለጣፊ ስሞችን በመስጠት ለማስፈራራት እየሞከረ መሆኑን ከአዲስ አበባ ዘጋቢያችን አስታውቆናል።
የነጋዴው ማህበረሰብ በተደጋጋሚ የዘረኛው ቡድን ሰለባ ሆኖ መቆየቱ ቢታወቅም የእህል ዋጋ ንረትን ለመቆጣጠር በሚል ስም አብዛኛዎቹን ነጋዴዎችን ከጫዋታ ውጪ እንዳደረጋቸው መግለጻችን ይታወሳል።ይህ አልበቃ ብሎት ለነሱ የማይጠግብ ኪስ መሙያ የሚሆን ገንዘብ ለማሰባሰብ አዲስ እቅድ አወጣን በማለት እየተሩዋሩዋጡ መሆናቸው የሚታወቅ ሲሆን ለዚህም ተባባሪ በመሆን ገንዘብ የሚረዲዋቸውንና የነሱ ደጋፊዎች የሆኑትን ልማታዊ፡ ግዴታቸውን የሚወጡ ባለሀብቶች በማለት የሚያሞካሻቸው ሲሆን ከግብር ጀምሮ የተለያየ ጥቅማጥቅሞችን እንዲያገኙ እያደረጉ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ መብታቸውን ለመጠቀም የሞከሩትንና የዚህና የዚያ ብሄር አባላት ናቸው በሚል የከፈሉዋቸውን ነጋዴዎች ጥገኛ፡ ግዴታቸውን የማይወጡ ባለሃብቶች በማለት እያገለሉዋቸው መሆኑ ታውቁዋል። ለነዚህም ነጋዴዎች በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ግብር እንዲጨምርባቸው አጋጣሚዎችን ሁሉ በመጠቀም በፍርድ ቤት የሚያንገላቱዋቸው መሆኑን ሪፖርተራችን አስታውቆናል።
ሪፖርተራችን በጉዳዩ ላይ ያናገራቸው አንድ ባለሀብት ከገንዘብም በላይ የገዢው ብድን አባላት በተለያየ ጊዜ በንግድና በመኖሪያ ቦታቸው በመሄድ የተለያየ ዛቻ እንደሚደርስባቸው ገልጽው ጉዳዩ ለህይወታቸውም እንደሚያሰጋቸው ተናገረዋል። በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን የሰጡ አንድ የፖለቲካ ተንታኝ ደግሞ ችግሩ ዛሬ የተጀመረ እንዳልሆነ እና ወያኔ ስልጣኑን ከተቆጣጠረ ጀምሮ ሲተገብረው የቆየው ገበያውንና ሀገሪቱን በአንድ ቡድን ቁጥጥር ስር የማዋል እቅድ አካል መሆኑን ገልጸዋል። ዘረኛው ወያኔ የሚፈጽመውን አድልኦ ተቁዋቁመው እስካሁን የቆዩትን ባለሃብቶች ጭራሽኑም ስራቸውን ለአገዛዙ የንግድ ድርጅቶች አስረክበው እንዲወጡ የታቀደ መሆኑን ተናግረዋል።
ይሕ በእንዲህ እንዳለ ሰሞኑን ዘረኛው የወያኔ አገዛዝ ያወጣው የዋጋ ተመን በሁሉም ነጋዴዎች ላይ እኩል ተግባራዊ እየሆነ እንዳልሆነ ሪፖርተራችን ነዋሪዎችን በመጠቆም አስታውቆናል። በተለያዩ የመዲናዋ ቦታዎች በመዘዋወር የከተማ ነዋሪዎችን ያናገረው ዘጋቢያችን ቁጥራቸው እጅግ ብዙ የሚሆኑ ነጋዴዎች ከተመን በላይ ሽጣችሁዋል በመባል የንግድ ቤታቸው እየታሸገ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ የገዢው ቡድን አባላትና ደጋፊዎች በመሆናቸው የሚታወቁ ባለሃብቶች እስካሁን ያለምንም ችግር ከዚህ ቀደም በነበረው ዋጋ እየሸጡ መሆናቸውን ገልጾልናል።
ነዋሪዎቸ እንደምሳሌ ያነሱዋቸውና ከተመን በላይ በመሸጥ ላይ አሉ ያሉዋቸውን ባለህብቶች ሳይቀር የዘረዘሩ ሲሆን በግንባር ቀደምትነት ግን በመዲናዋ 22 ተብሎ በሚታወቀው ስፍራ ሆሊውድ በመባል የሚታወቀው ባር ቢራ በ 15 ብር እየሸጡ መሆኑን ጠቅሰው ይህም እንደምሳሌነት ተነሳ እንጂ ድርጊቱ በሁሉም መጠጦች ላይም መሆኑን ጠቁመዋል።
ይህ አድሎአዊ አሰራር በርግጥ ዘረኛው ወያኔ የገዢው አባል ያልሆኑትን የንግዱን ማህበረሰብ ከስራ በማባረርና ራሳቸው በመቆጣጠር የሀገሪቱን ህብት ለመዝረፍ ያመቻቸው ዘንድ ያቀዱት የረዢም ጊዜ እቅድ መሆኑን ቁልጭ አድሪጎ የሚያሳይ ነው። ከዚህ ቀደምም በከተማይቱ የግብርን ተመን ለማሻሻል በማለትና በየ ባለህብቱ የንግድ ስፍራ በመዞር ምክንያታዊ ያልሆነና በግልጽ በዘርና በፖለቲካ አመለካከት ላይ የተመሰረተ ተመን ሲጣል መቆየቱ በዚህም ብዙ ባለሀብቶች ለነፍሳቸው በመፍራት ሀገር ጥለው እንዲሰደዱ መደረጋቸው ይታወቃል።