በዘረኛውና አምባገነኑ አገዛዝ የሽብርተኞችን ደባ አከሸፍኩ በማለት ሲደነፋ መሰንበቱ ተዘገበ
በዘረኛውና አምባገነኑ መለስ የሚመራው የወንበዴ ቡድን በቁጥጥሩ ስር በሚገኘው የመገናኛ ብዙሀን ተሸርቦብኝ የነበረውን ጥቃት በተሳካ መልኩ አከሸፍኩ በማለት ሲደነፋ መሰንበቱን ዘጋቢያችን ከስፍራው በላከልን ሪፖርት አስታውቆናል።
እንደዘገባው ዘረኛው የወያኔ አገዛዝ በቁጥር ሰባት የሚሆኑ የተባሉ ሽብርተኞች ከኤርትራ መንግስት የገንዘብና የስልጠና ድጋፍ ሲሰጣቸው የቆዩ መሆናቸውን ጠቅሶ በአፋር ክልል በኩል ወደ ኢትዮጵያ ሰርገው እንዲገቡና ሰላም እና አለመረጋጋት እንዲፈጠር እንዲያደርጉ የተላኩ ናቸው ሲል ከሱዋል። ዘረኛው አገዛዝ አያይዞም ሽብርተኛ ተብዬዎችን በቁጥጥር ስር ሲያውል በእጃቸው ላይ ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ፣ የነፍስ ወከፍ መሳሪያና ከባድና ቀላል ፈንጂዎችን እንደያዘ ጠቅሱዋል። ተቆጣጥሮት ባለው የቴሌቪዚን ጣቢያም አንደኛውን ሽብረተኛ ተብዬ ያቀረበ ሲሆን ሰውዬውም የወያኔው አገዛዝ እንዳለው ከኤርትራ መንግስት ለሽብር ስራ የተላከ መሆኑን መናገሩም ታውቁአል።
ይሁን እንጂ የዜናውን እውነተኛነት ለማጣራት ሽብርተኞች ናቸው የተባሉት በቁጥጥር ስር ዋሉባቸው በተባሉት የአፋር ጠረፋማ አካባቢዎች የተንቀሳቀሰው ዘጋቢያችን ወሬው ፈጽሞ ከእውነት የራቀና የፈጠራ መሆኑን የካባቢውን ነዋሪዎች ጠቅሶ ዘግቦአል። ለዘጋቢያችን ስማቸው እንዳይጠቀስ በመጠየቅ አስተያየታቸውን የሰጡት አንድ ያካባቢው አዛውንት ጉዳዩ ወያኔ ከገባ ጀምሮ በአፋር ህዝብ ዘንድ ተቀባይነት ያላገኘውና ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተጠናከረ በመጣው ተቃውሞ የተደናገጠው መለስ አካባቢውን ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር አውዬዋለሁ የሚል ስሜት በህዝቡ ዘንድ በመፍጠር ህዝቡን ለማስፈራራት የተጠቀመበት ዘዴ መሆኑን ተናግረዋል። አዛውንቱም በመቀጠል ወያኔ ከፍርሃቱ የተነሳ በክልል አዛውንት ሴቶችና ህጻናት ሳይቀሩ ሲያስር ሲገርፍና ሲገድል የቆየ መሆኑን ጠቅሰው ሽብርተኛ ከተባለም ከወያኔ በላይ ማን አለ ማለታቸውን ዘጋቢያችን ገልጽዋል፡፡
ወያኔ ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ በኦሮሚያ እና በ ሶማሌ አካባቢ ላይ በማተኮር የኦንግ እና የ ኦብነግ ደጋፊ ናችሁ በማለት በንጹሀን ዜጎች ላይ ግፍ ሲፈጽም መቆየቱ የሚታወቅ ሲሆን በተደጋጋሚም በሽብር ስራ ላይ ሊሰማሩ ሲሉ አገኛሁዋቸው በማለት የራሱን ሰዎች መሳሪያ በማሲያዝ በሚቆጣጠረው የቴሌቪዚን ጣቢያ ሲያቀርብ መቆየቱ የሚታወስ ነው።