በደቡብ ኦሞ የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞች ዘረኛውን መለስ ዜናዊ መቀበያ ከደሞዛቸው 20 በመቶ እንዲያዋጡ ተጠየቁ፣ መምህራን አሻፈረኝ ብለዋል
ከደቡብ ኦሞ ዋና ከተማ ጂንካ የተገኘው ዜና እንደሚያመለክተው የወያኔው ቁንጮ መለስ ዜናዊ በቅርቡ አከባቢውን ለመጎብኘት ማቀዱን እና ለእርሱ መቀበያ እያንዳንዱ የመንግስት ሰራተኛ ከደመወዙ 20 በመቶ በግዴታ እንዲያዋጣ ትዕዛዝ መተላለፉን ፣ የተጠየቀውን ገንዘብ የማያዋጡ የመንግስት ሰራተኞች ካሉ ደግሞ የዲሲፕሊን እርምጃ እንደሚወሰድባቸው ማስፈራሪያ አዘል ማስጠንቀቂያ መሰጠቱን ለማወቅ ተችሎአል።
ይህንን በወያኔ አሽቃባጮች የተሰጠውን ማስጠንቀቂያ ተከትሎ የክልሉ መምህራን ገንዘብ ለማዋጣት ፈቃደኞች አለመሆናቸውን ያስታወቁ ሲሆን፣ ባካባቢው ካድሬዎችና በመምህራኑ መካከል ከፍተኛ ውዝግብ መነሳቱን ያካበባው የመንግስት ሰራተኞች ለኢሳት ዜና ወኪል መግለጻቸውን የኢትዮጵያ ሳታላይት ቴለቪዝን ከትናንት በስትያ ማክሰኞ የዜና ክፍለ ጊዘው አስታውቆአል።
ደቡብ ኦሞ በሁሉም ረገድ ወደሁዋላ የቀረ አካባቢ መሆኑን የሚናገሩት ሰራተኞች፣ በግንቦት97 ምርጫ ወቅት የአካባቢው ህዝብ ሙሉ በሙሉ ቅንጅትን በመምረጡ ምክንያት ከወያኔ ጋር ሆድና ጀርባ ሆኖ መቆየቱን ይናገራሉ።
ወያኔ መላውን አገሪቱን ለመዝረፍ በዘረጋው ስልት በሃይል ያገኘውን ስልጣን ለመቆጣጠር እንዲያመቸው በመንግሥት ሥራ ላይ የተሰማሩትን ሁሉ በማስገደድ የወንጀለኛ ድርጅቱ አባል እያደረገ መሆኑ ሲታወቅ ፤በደቡብ ኦሞ ክልልም እንደተቀረው ያገሪቱ ክፍል አባል ላለመሆን የሚያንገራግሩት ሁሉ በቢፒአርና በግምገማ ስራቸውን እንዲለቁ እያደረገ መሆኑን ብዙዎች ግን መሄጃና ምርጫ ከማጣት የተነሳ በልባቸው ወያኔ /ኢህአዴግን አጥብቀው የሚጠሉ ቢሆኑም ለእንጀራቸው ሲሉ አባል ለመሆን መገደዳቸውን ገልጸዋል።
ደቡብ ኦሞ እጅግ ኋላ ቀርና ድህነት ያጎሳቆለው አካባቢ እንደሆነ ሲታወቅ የዘረኛው መለስ ዜናዊ ጉብኝት ዓላማ ምን እንደሆነ በካድሬዎቹ በኩል የተገለጸ ነገር የለም ። የኑሮ ውድነት ከመሃል አገር እስከ ጠረፍ በተዛመተበት እና የመንግሥት ሠራተኛ የሚከፈለው የወር ደመወዝ ለዕለት ጉርሱ አንኳ እንደማይበቃ እየታወቀ የወያኔ ካድሬዎች ሰበብ እየፈለጉ ህዝቡ ከጉሮሮው ነጥቆ እንዲያዋጣ የሚጠይቁት ገንዘብ ከፍተኛ ብሶት እየቀሰቀሰ እንደሚገኝ ለኢሳት ወኪል የተናገሩት ሰዎች ለመለስ መቀበያ ገንዘብ አናዋጣም ያሉት የኦሞ መምህራን በያዙት አቋም ለምን ያክል ጊዜ እንደሚገፉ ባይታወቅም፣ ሌሎች የመንግስት ሰራተኞች ግን ወያኔን መጋፋት ፈርተው ደሞዛቸውን ማስቆረጥ ጀመረዋል ብለዋል ።