ወያኔ የደገሰው የባንዲራ ቀን በዓል በታሰበው መንገድ ሳይከበር ቀረ

ዘረኛውና አምባገነናዊው የወያኔ አገዛዝ ያዘጋጀው የባንዲራ ቀን በዓል በህዝቡ ትኩረት ሳይሰጠው ማለፉ ታውቋል።

የኢትዮጵያ ባንዲራ በወያኔ አገዛዝ ዘንድ የሚንቋሸሽ እንደሆነና ዘረኛው አምባገነን መለስ ዜናዊ ስልጣን እንደተቆጣጠረም ባንዲራው ከጨርቅ ያለፈ ዋጋ እንደሌለው መናገሩ ይታወሳል።

ይሁን እንጂ ከተወሰነ ጊዜ ወዲህ አገዛዙ እራሱን እንደ አርበኛ ኢትዮጵያዊ ድርጅት ቀርጾ ህዝቡን ለማታለል ከሚያደርገው ጥረት ጋር አያይዞ የባንዲራ ቀን መሰየሙ ይታወቃል። የዚህ አመቱ በዓልም ሰኞ መስከረም 10፣ 2003 ቀን የተከበረ ሲሆን፤ የወያኔን ቀጣፊነት የተረዳው ህዝብ ለበዓሉ ትኩረት እንዳልሰጠው የግንቦት 7 ዘጋቢ ከአዲስ አበባ አጠናቅሮ በላከው ዘገባ ገልጿል። ከአገዛዙ ካድሬዎች በስተቀር በዓሉን ለማክር የወጡት እንኳ ተገደው እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።