የአዲስ አበባ አሽከርካሪዎች በአገዛዙ የትራፊክ ፖሊሶች በደል እየደረሰብን ነው በማለት አማረሩ
የወያኔው አምባገነን አገዛዝ የትራፊክ ፖሊሶች ፍጹም አግባብነት በሌለው መልኩ ያለምንም ምክንያት ቅጣት እየቀጧቸው መሆኑን ና በዚህም ምክኒያት እጂግ እየተማረሩ መሆናቸውን በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ አሽከርካሪዎች ለዘጋቢያችን ገለጹ።
እንደ ዘጋቢያችን ሪፖርት ይህ ችግር በአብዛኛው ጎልቶ የታየው በታክሲ አሽከርካሪዎች ላይ መሆኑንና የትራፊክ ፖሊሶቹ ለአገዛዙ ገንዘብ በዚህ መንገድ ሰብስቡ የተባሉ እስኪመስሉ ድረስ ምንም ስህተት ባልተሰራበት ሁኔታ ቅጣት እየቀጧቸው መሆኑ በጂጉ እንዳበሳቻቸው ተናግረው ፖሊሶቹ ያላግባብ አሽከርካሪዎቹን ሲቀጡ አቤት የሚባልበትም ሆነ የሚዳኙበት አለመኖሩ ደግሞ ሌላው አሳዛኝ ነገር እንደሆነባቸው ተናግረዋል።
ዘረኛውና አምባገነኑ የወያኔ አገዛዝ በሃገራችን የተለያዩ ሴክተሮች ፍጹም የሆነ ዝርክርክነትና በሙስና የተዘፈቀ አሰራርን ሲያሰፍን መቆየቱንና እያሰፈነ ያለ መሆኑን በተደጋጋሚ ስንዘግብ መቆየታችን አይዘነጋም፡፡