ግንቦት7 የዘረኛውን አምባገነን መለስ ዜናዊ የ እንነጋገር ጥሪ የተለመደ ቅጥፈት ነው ሲል አጣጣለው
ዘረኛው የወያኔ አገዛዝ ቁንጮ የሆነው መለስ ዜናዊ ለአገር ውስጥ ጋዜጠኞች በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ፡ ህገመንግሥቱን ተቀብለው በሰላማዊ መንገድ መንቀሳቀስ እስከ ተስማሙ ድረስ ከማንኛውም ሃይል ጋር ለመደራደር እንደሚፈልግ ገልጾ በሃይል ከስልጣን ሊያባሪሩኝ ነው እያለ ዘወትር ከሚከሳቸው የግንቦት7 እና የ ኦሮሞ ነጻነት ግንባር ጋርም ለመነጋገር ዝግጁ እንደሆነ መናገሩን ጋዜጣዊ መግለጫውን የተከታተሉ የተለያዩ የዜና አውታሮች መዘገባቸው ይታወቃል።
ይህንን አስመልክቶ የግንቦት 7 ን አቋም እንዲገልጹልን የዝግጅት ክፍላችን ያነጋገራቸው የንቅናቄው ሊቀመንበር ዶ|ር ብርሃኑ ነጋ የወያኔ መሪዎች በተለይም በቅርበት የሚያውቁት መለስ ዜናዊና ጥቂት ግብረበሮቹ የሥልጣን ዕድሜያቸውን የሚያራዝም መስሎ እስከታየቸው ድረስ አደባባይ ላይ ቆሞ መዋሸትን እንደነውር የሚቆጥር ህሊና ስለሌላቸው የሚናገሩትን ወይም ቃል የሚገቡትን ነገር ከምር የሚወስድ ኢትዮጵያዊ የለም ስሉ አጣጥለውታል።