መድረክ ምርጫውን የሚገመግም ኮሚቴ አቋቋመ

– ድርጅቱ ወደ ግንባር ሲሸጋገር አንድ ወጥ አመራሮች ይኖሩታል

(በኃይሌ ሙሉ)

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ (መድረክ) ጠቅላላ ጉባዔ የ2002 ምርጫን የሚገመግሙ ስድስት አካላት ያሉት ኮሚቴ እንዲቋቋም ውሳኔ አስተላለፈ፡፡ ድርጅቱ ወደ ግንባር ሲሸጋገር የአመራር አባላቱ የሥልጣን ጊዜ ወጥ ይሆናል ተባለ፡፡