ኢንጂነር ኃይሉ የድርጅታቸውን ችግር አፅድተው ሥልጣን እንደሚለቁ አስታወቁ
– ‹‹ከመተዳደሪያ ደንቡ ውጪ የሚሠራ ሥራ በዝቷል›› ዶ/ር ታዲዮስ ቦጋለ
በታምሩ ጽጌ
የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ፕሬዚዳንት ኢንጂነር ኃይሉ ሻውል በቅርቡ በፓርቲው ውስጥ የተፈጠረውን ችግርና አለመግባባት ካስተካከሉና ካፀዱ በኋላ፣ ከፕሬዚዳንትነታቸው እንደሚሰናበቱ መጋቢት 1 ቀን 2003 ዓ.ም. በጽሕፈት ቤታቸው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታወቁ፡፡