ለነዳጅ ዋጋ ጭማሪው መፍትሔ ድጎማ ወይስ ታክስ ቅነሳ?

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የነዳጅ ዋጋ በአሳሳቢ ሁኔታ እያሻቀበ ነው፡፡ በሊቢያ የተከሰተው ሕዝባዊ አመፅ የበለጠ በመካረሩ፣ በቀን 1.6 ሚሊዮን ነዳጅ ለዓለም ገበያ የምታቀርበው ሊቢያ የነዳጅ ምርቷ ተስተጓጉሏል፡፡