ቶፕ ቪው እንጦጦ ዋሲሁን አርት ጋለሪ ለአካባቢ ባለሥልጣን ተሰጠ

– ባለቤቱ መንግሥትን ድረስልኝ እያሉ ነው

በታምሩ ጽጌ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ኤልያስ ራጉኤል (እንጦጦ አፋፍ) የሚገኘውና በስዕል ማሳያነት ላለፉት ስምንት ዓመታት ሲያገለግል የነበረው ቶፕ ቪው እንጦጦ ዋሲሁን አርት ጋለሪ ለአዲስ አበባ አካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ተሰጠ፡፡