የሸራተን አዲስ ሠራተኞችና ማኔጅመንት በአገልግሎት ክፍያ እየተወዛገቡ ነው

በታምሩ ጽጌ

የጥቅምት ወር 2003 ዓ.ም. የአገልግሎት ክፍያ (ሰርቪስ ቻርጅ) ሳይከፈላቸው በመቅረቱ በሠራተኛ ማኅበሩ በኩል ‹‹ለምን አልተከፈለንም?›› በሚል ጥያቄ ያቀረቡ የሸራተን አዲስ ሆቴል ሠራተኞችና ማኔጅመንቱ እየተወዛገቡ ነው፡፡