ፀረ ሙስና ኮሚሽን ከ1.9 ሚሊዮን ካሬ ሜትር በላይ መሬት በፍርድ ቤት አሳገደ

– ሀብታቸውን ያሳወቁና ያስመዘገቡት አራት ባለሥልጣናት ብቻ ናቸው

(በታምሩ ጽጌ)

የፌዴራል የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን በመሬት ዙሪያ የተፈጸመውን የሙስና ወንጀል መመርመር ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ እስከ 2003 ዓ.ም. ሩብ ዓመት ድረስ፣ ከ1 ሚሊዮን 974 ሺሕ 787 ካሬ ሜትር በላይ ስፋት ያለው መሬት በፍርድ ቤት ትዕዛዝ እንዲታገድ ማድረጉን አስታወቀ፡፡