ሙክታር ከድር ብርሃኑ አዴሎን ተኩ

ቀደም ሲል የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ጽሕፈት ቤትና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር የነበሩት አቶ ብርሃኑ አዴሎ ተነስተው፣ በቦታቸው ከመስከረም 26 ቀን 2003 ዓ.ም. ጀምሮ አቶ ሙክታር ከድር በሚኒስትር ማዕረግ መሾማቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡