በመጪዎቹ አምስት ዓመታት የግብርናው ዘርፍ 75 ቢሊዮን ብር በጀት ይፈልጋል

– 3.3 ሚሊዮን ሔክታር መሬት ለባለሀብቶች ለማስተላለፍ ዕቅድ ተይዟል

(በዳዊት ታዬ)

የግብርናና ገጠር ልማት ሚኒስቴር በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት የግብርና ዘርፉን ልማት ለማሳካት ከ75 ቢሊዮን ብር በላይ በጀት የሚያስፈልገው መሆኑ ተመለከተ፡፡