መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎቹ አድማቸውን ካላቆሙ ይባረራሉ አለ
(በምዕራፍ ብርሃኔ)
የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ከህዳር 8 ቀን 2003 ዓ.ም. ጀምሮ የምግብና የትምህርት አድማ የመቱ ከመቶ በላይ የሆኑ ተማሪዎችን (ደቀመዛሙርት) ወደ ትምህርት ገበታቸው የማይመለሱና ከሆነና የኮሌጁን ምግብ የማይመገቡ ከሆነ፣ የኮሌጁን ንብረት አስረክበው ክሊራንስ በማስፈረም የትምህርት ተቋሙን በአስቸኳይ ለቀው እንዲወጡ ከትናንት በስቲያ አስታወቀ፡፡