አዲስ አበባ ላይም መፍትሔ ያጣው የአቤይ ግዛት ስጋት

(በኃይሌ ሙሉ)

በሱዳን መንግሥትና በሱዳን ሕዝቦች ነፃነት ንቅናቄ መካከል የተፈረመው ሁሉን አቀፍ የሰላም ስምምነት አፈጻጸምንና በሶማሊያ ጉዳይ ላይ ለመወያየት ትናንት በአዲስ አበባ ሸራተን አዲስ የተሰበሰቡት የምሥራቅ አፍሪካ በይነ መንግሥታት (ኢጋድ) መሪዎች፣ ዕምቅ የነዳጅ ሀብት ባላት አወዛጋቢዋ የአቤይ ግዛት ጉዳይ ላይ እልባት ሳይሰጡ ተለያይተዋል፡፡