ትራንስፖርት ባለሥልጣንና አንበሳ አውቶቡስ ወደ አዲስ አበባ እንዲመለሱ ተወሰነ

(በውድነህ ዘነበ)

ቀደም ሲል በፌዴራል ትራንስፖርት ባለሥልጣን መሥሪያ ቤት ሲመራ የቆየው የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤትና አንበሳ አውቶቡስ ድርጅት ወደ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እንዲመለሱ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ተወሰነ፡፡