የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተቀማጭ ገንዘብ ‹‹ድርቅ›› ሊያጋጥመው ይችላል
(በጋዜጣው ሪፖርተር)
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተቀማጭ (Deposit) ከያዘው 57 ቢሊዮን ብር ውስጥ ከ30 ቢሊዮን ብር በላይ ለኮንዶሚኒየም ቤቶች ግንባታና ለሌሎች ፕሮጀክቶች፣ ለመንግሥት የልማት ድርጅቶችና ለክልሎች በረዥም ጊዜ ክፍያ ሲያበድር፣ 20 ቢሊዮን ብር የሚሆን ደግሞ ለግል ድርጅቶችና ግለሰቦች ማበደሩ ታወቀ፡፡