በአትሌት ገዛኸኝ አበራ ትምህርት ቤት የሚኒስትሪ ውጤት እያወዛገበ ነው
(በታምሩ ጽጌ)
በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ሸዋ ዞን አዳበርጋ ወረዳ የሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ ሠራተኞች ልጆችና የአካባቢው ነዋሪዎች የሚማሩበት የገዛኸኝ አበራ ትምህርት ቤት የ8ኛ ክፍል ሚኒስትሪ ተፈታኞች ውጤት፣ ትምህርት ቤቱንና የዞኑን (አምቦ) ትምህርት ጽ/ቤት እያወዛገበ መሆኑን ያካባቢ ነዋሪዎች ለሪፖርተር ገለጹ፡፡