ኢትዮጵያና የጠፋው 8.5 ቢሊዮን ዶላሯ

እስክንድር ነጋ (አዲስ አበባ)

ክፍል አንድ

 

ትላንት፣እሁድ፣ ግንቦት 142ዐዐ3 .ም፣ የእናቴን አርባ አወጣኹ። ውስጤ የፈጠረውን ስሜት ልገልፀው አልችልም። ደስታ አይደለም፡፡በውስጤ ያለው ባዶነት ደስታን ውጦ የሚያስቀር ጨለማ ጉድጓድ ነው። እርካታ ብለው የተሻለ ይመስለኛል። የእናቴ ነፍስ ከእንግዲህ የፍርድ ቀንን በሰላም መጠበቅ ትችላለች ብዬ አስባለኹ።