ታክሲዎች ስራ ማቆም አድማ እንድምታ

እስክንድር ነጋ (አዲስ አባባ)

 

አስኮ፣ ላፍቶ፣ ለቡ፣ ኤአት ፣ ሲ.ኤም.ሲ፣ ዓለም ባንክ፣ ቀራንዮ፣ ኮተቤ፣ ቃሊቲ… የማለዳ ታክሲ ለወትሮውም መከራ ነው። ግፊያው የድብድብ ያህል ነው። ትላንት ሰኖ ግምቦት 8/2003 ግን ፣ ተጋፍቶ የሚገባበት ታክሲ የጠፋው ገና ከጠዋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ ነበር። የአንድ አዓቱን ግፊያ እየሸሸ ቀደም ብሎ ከቤቱ የሚወጣው የከተማው ነዋሪ ታክሲዎች ምር አድማ መተዋል ብሎ መጠርጠር  የጀመረው የወትሮ ደምበኞቹ የውሃ ሽታ ሆነው ሲቀሩበት ነበር። የቻለ እንደ ሰርዲን በሞጠቀጠቁት አውቶቢሶች ላይ እንደምንም ተሰጉጦ አመለጠ። ከፊሉ በእግሩ አስነካው። እድለኛው የቤት መኪና እየተባበረው በምቾት ወደ መሀል ከተማ ዘለቀ። ብዙዎች ከስራና ከትምህርት ቀርተው ወደቤታቸው ተመለሱ።