አቤት ውሸት! አቤት ውሸት! (ወንድሙ መኰንን)

ወንድሙ መኰንን (ሎንደን መጋቢት 2003 ዓ.ም.)

ወያኔ የውሸት ቋት ነው። የወያኔ ውሸት ስልችት ያለው ኢትዮጵያዊ በእብለቱ ዙሪያ ቀልድ እየቀለደ የባዶ ሆዱን በሳቅ ያስታግሳል። አንዱ ቀልድ የ42 ኢንቸ ጠፍጣፋ ቴሌቭዥን ወያኔ በዋሸ ቁጥር እየተሸማቀቀ እየተሸማቀቀ ተኮራምቶ ወደ አንዲት ብልጭ፣ ድርግም የምትል 15 ኢንች መለወጡ ነው። ምን ወያኔ ያልዋሸው አለ? ከሻዕቢያ ጋር አብሮ የወጋ እኮ ነው! ምነው ቢባል፣ ”ደርግን አስወግጄ ዴሞክራሲ ላመጣ ነው” አለን። አቤት ውሸት! አቤት ውሸት! ድንቄም ዴሞክራሲ! አሁንም አፈናው ከደርግ የበለጠ እንጂ፣ ያነሰ አለመሆኑን እንደነቃንበት ያውቅ ይሆን?!