ኢትዮጵያ ግብጽ አይደለችም – አንድ ተብሎ የሚጀመረው
ናኦሚ በጋሻው – ሎንግ ቢች ካሊፎርኒያ ([email protected])
በግብጽና በቱኒዚያ የታየውን ህዝባዊ እንቅስቃሴ እንደ ምሳሌ በመጥቀስ፣ ድርጅታዊ ሥራ ሳይሠራ የኢትዮጵያ ህዝብ ከዛሬ ነገ ሊነሳ ይችላል ብለው ብዙዎች ይጠባበቃሉ። እነዚህ ሰዎች እንደጠበቁትም ህዝቡ ሊነሳ ይችላል። የወደፊቱን እንዲህ ነው ብሎ በርግጠኝነት ለመተንበይ ይከብዳል። ነገር ግን ያለውን ሁኔታ ከተለያዩ አቅጣጫዎች ስናያቸው አሁን ባለው ሁኔታ ህዝቡ የሚነሳ አይመስልም።