ኢትዮጵያ፡ ሕዝባዊ ተቃውሞና የወታደራዊ መንግሥት ጥያቄ
እስክንድር ነጋ
የደርባባውና የ82 ዓመቱ አዛውንት ሆስኒ ሙባረክ ከስልጣን መውረድ ዓርብ አመሻሽ ላይ ሲበሰር፣ በግብፅ ታሪክ ተሰምቶ የማይታወቅ እልልታና ሆታ ቀለጠ… ሕዝብ በደስታ ሰክሮ ሌሊቱን አሳለፈ…. አይ ካይሮ ያቺን ምሽት!… እንዴት ትረሳለች?… እኛስ አብረናቸው አላደርንም እንዴ?… ዕድሜ ለአልጀዚራ፣ ለቢ.ቢ.ሲ፣ ለሲ.ኤን.ኤን፣ ለፕሬስ ቲቪ… የካይሮ ሕፃናት እንዴት ይረሱናል?… ገብቷቸው ይሆን እንዲያ የፈነጠዙት?… ጨለማውን ብርሃን እንደዋጠው እውን ለእነሱም ታይቷቸው ነበርን?… ቀልባቸው ነግሯቸው ይሆን?… የትላልቆቹማ ምኑ ይወራል… በእነሱ ደስታ እኛም እምባ ተራጭተናል…