ኮሎኔል ታደሰ ሙሉነህ በኤርትራ ፀጥታ ሀይሎች ታፍነው የደረሱበት አልታወቀም
በኤርትራ ያሉ የኢትዮጵያ ታጋዮች ስጋት ላይ ናቸው
Ethiopia Zare (ቅዳሜ ኅዳር 25 ቀን 2003 ዓ.ም. December 4, 2010)፦ የቀድሞ የኢትዮጵያ አየር ሀይል ባልደረባና ከጥቂት አመታት በፊት የአርበኞች ግንባር መስራችና ምክትል ሊቀመንበር፡ የነበረው ኮሎኔል ታደሰ ሙሉነህ፡ ከኦክቶበር 25 ቀን ጀምሮ በአስመራ ከመኖሪያ ቤታቸው ታፍነው ተወስደው መታሰራቸውንና እስካሁንም የደረሱበት እንዳልታወቀ በአስመራ የሚገኙ ምንጮቻችን ገለጹ።