ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች ከዚኽ ወዴት? (ክ. ዘጠኝ/አያልሰው ደሴ)

የኢትዮጵያ ህዝብ፣ አገር-ወዳድና ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች እና ኢህአዴግ፤ ከዚኽ ወዴት? ክፍል ዘጠኝ

አያልሰው ደሴ (የግል አስተያየት)

በዶ/ር በየነ ጴጥሮስ (የሐድያ ብሔር ዴሞክራሲያዊ ድርጅት) ሰብሳቢነት፣ በአቶ ከበደ ገብራይ (ኢዴኃቅ) ምክትል ሰብሳቢነት እና በዶ/ር ታዬ ወ/ሰማያት (የኢትዮጵያ መምህራን ማኅበር) ፀሐፊነት የተመራውና ከታኅሳስ ፱ እስከ ፲፫ ቀን ፲፱፻፹፮ ዓ.ም. በተካሄደው የአዲስ አበባው ”ሠላምና እርቅ በኢትዮጵያ ሀገር አቀፍ ጉባዔ” ውሳኔ መሠረት በጉባዔው ላይ ከተሳተፉት ውስጥ ሰላሣ አንድ የፖለቲካ ድርጅቶችና የሙያ ማኅበራት በተገኙበት ታኅሳስ ፳፩ ቀን ፲፱፻፹፮ ዓ.ም.የኢሰዴአኃ ምክር ቤትን መመስረታቸው ይታወቃል።