ይድረስ ለዕጩ ’ጠቅላይ ሚንስትራችን’ ኃይሌ ገ/ሥላሴ (ነፃነት ዘገዬ)

ነፃነት ዘገዬ

የኢትዮጵያን ወቅታዊ ጉዳይ ይሁነኝ ብሎ ለሚከታተል የውስጥም ሆነ የውጭ ታዛቢ በየዕለቱ አዳዲስ አስገራሚ ነገር አያጣም። ”ቀን የሰጠው ቅል …” እንዲሉ ጊዜ የሰጠው ሞልፋጣ ሁሉ ባልተገራ ስድ አንደበቱ ህዝብን ባገኘው አጋጣሚና መድረክ እየተነሳ ሲሳደብ መስማት ደግሞ የዘመናችን ፍሽን ሆኖ ከመገኘቱም በላይ ይህ በአሳዛኝነቱ ከሁሉም የሚበልጥ ሀገራዊ ጉዳይ ’ሃይ’ የሚለው ማጣቱ ይበልጥ ያስገርማል።