ብርቱካን ሚደቅሳ ከነማንዴላና አንሳ ሱንኪ ምድብ ልትገባ ነው

ግርማ ካሣ ([email protected])

ሐምሌ 27 ቀን 1981 ዓ.ም. ነበር። በአደባባዩ የሰፈረው በመቶ ሺ የሚቆጠር ሕዝብ የተለያዩ መፈክሮችን ይዞ ”እምቢ አምባገነንነትን! እምቢ የአንድ ፓርቲ ሥርዓትን! እምቢ የሰብዓዊ መብት ረገጣን” እያለ ይጮሃል። ታንኮችንና መትረየሶች የተደቀኑባቸው የወታደር መኪናዎችን በማሰማራት፣ የአገሪቱ 27ኛው ክፍለ ጦር ህዝቡን ከቧል። ታንኩ እየቀረበ መጣ። አንድ ወጣት ከታንኩ ፊት ቆመ። ታንኩ ጨፍልቆት አለፈ። ድንገትም ተኩስ ተጀመረ። መሳሪያ በታጠቁ በአገራቸው ሰዎች በተተኮሰ ጥይት በሺሆች የሚቆጠሩ ወደቁ። የሰው ልጆች ደም እንደ ጎርፍ ፈሰሰ።