… ኢህአዴግ፤ ከዚኽ ወዴት? (ክፍል ስድስት – አያልሰው ደሴ)

የኢትዮጵያ ህዝብ፣ አገር-ወዳድና ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች እና ኢህአዴግ፤ ከዚኽ ወዴት? ክፍል ስድስት

አያልሰው ደሴ (የግል አስተያየት)

ሐ-፩፦ የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች ቅንጅት (ኢዴኃቅ) …፣

በተጨማሪም ከዚኽ በላይ እንዳየነው ኢዴኃቅ እንደኢትዮጵያዊ ድርጅቶች ስብስብ ኢህአዴግ በኢትዮጵያ ላይ የተያያዘውን የጥፋት አቅጣጫ ለማስቀየርና ለሀገር አንድነትና ለህዝባዊ ሥርዓት እውን መሆን የሚያደርገው ትግል ሁሉ-አቀፍ እንዲሆንና የበለጠ እንዲጎለብት በማሰብ፣ በሱ (በኢዴኃቅ) ውስጥ ያልተካተቱና በሀገሪቱ ላይ ለውጥ እንዲመጣ የሚሹ ፀረ-ኢህአዴግ ኃይሎች እንዲሰባሰቡ ያልተቋረጠ ጥረት አድርጓል።