… ከዚኽ ወዴት? (ክፍል አምስት – አያልሰው ደሴ)
የኢትዮጵያ ህዝብ፣ አገር ወዳድና ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች እና ኢህአዴግ ከዚኽ ወዴት?
ክፍል አምስት (ከክፍል አራት የቀጠለ)
አያልሰው ደሴ (የግል አስተያየት)
ሐ-፩፦ የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች ቅንጅት (ኢዴኃቅ)
በአገራችን የተደራጀ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ታሪክ የተለያዩ ፖለቲካዊ አመለካከቶችና ፍልሥፍናዎችን የሚከተሉ፣ አልፎም ተፃራሪ አስተሳሰቦችን የያዙና በተመሳሳይ የፖለቲካ ቅኝት ውስጥም ሆነው ነፍስ እስከመጠፋፋት በደረሰ ሁኔታ በምር ጠላትነት የተፈራረጁ የፖለቲካ ድርጅቶችን በአንድ ጠረጴዛ ዙሪያ ከማስቀመጥ አልፎ በጋራ ለመታገል ቆርጠው የጋራቸው የሆነ ድርጅት መሥርተው በአንድነት የታገሉበት የመጀመሪያው የጋራ የትግል መድረክ የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች ቅንጅት (ኢዴኃቅ) ነው።