በውሸት ደዌ ለምትሰቃዩ – እነሆ እውነቱን! የአፍሪካም ጭራ ነን (ሲሳይ አጌና)

ሲሳይ አጌና – ከአዲስ አበባ

ከአምስት አመት በፊት 1997 ኢትዩጵያ ዲሞክራሲን አማጠች፤ የተስፋ ብርሃንም ተንቦገቦገ፤ ኢትዮጵያ ሚያዚያ 30 የጀመራትን ምጥ ግንቦት 7/97 ተገላገለች። ዲሞክራሲ ተወለደ። ግንቦት 7 አመሻሹላይ ህጻኑ ዲሞክራሲ ህመም ጀመረው፤ በማግስቱም ህመሙ ጸናበት፤ ህጻኑ አንዴ እየተሻለው ሌላ ጊዜ ደግሞ እየበረታበት ግንቦት 29 ሀወመሙ አጣደፈው፤ ግምቦት 30 ይበልጥ በረታበት፤ ሰኔ አንድ ቀን ነፍሱ አልወጣ አለች እንጂ በድን ሆነ። አዎ ህጻኑ የኢትዮጵያ ዲሞክራሲ በ “ኮማ” (ሰመመን) ውስጥ ለአራት ወራት ያህል ቆይቶ ጥቅምት 22/98 ዓ.ም አሸለበ። ሁሉም ነገር ወደ ኋላ ተመለሰ።