የአባዩ ሕዳሴ ግድብና በዙሪያው ያሉ ንግግሮች
“አባይ መገደብ አለበት” በሚለው ሃሣብ ላይ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ይስማማል፡፡ ተቃዋሚዎች እንደሚሉት የግድቡ ግንባታ አሁን በድንገት በኢትዮጵያ መንግሥት መነሣቱና እነርሱን ያገለለ የገዥው ፓርቲና ደጋፊዎቹ ብቻ ፕሮዤ ሆኖ መታየቱ፣ ግድቡ በዓይነቱ ግዙፍ መሆኑና የሚያስፈልገው ወጭ ከፍተኛነት፣ ለዚህም ሕዝብ `ቦንድ ግዛ` መባሉ እያወያየ ነው፡፡
ገዥው ፓርቲ ኢሕአዴግና ደጋፊዎቹ `ግድቡ ኢትዮጵያን ከድኅነት ያላቅቃል፣ የግንባታው ሃሣብም አዲስ አይደለም፤ ውሎ ያደረ ነው፤ ድጋፍ ይገባዋል` ይላሉ፡፡
የሕዳሴ ግድብ ሥራን በተመለከተ ስለዕቅዱ ዓላማና ወቅታዊነት፣ ቴክኒካዊ አሠራሩን፣ ግንባታው ስለሚጠይቀው ወጪ፣ ከአጎራባች አገሮች በተለይም ከናይል ተፋሰስ አገሮች ጋር ባለው ግንኙነት ላይ የሚኖረው አንድምታ፣ ዕቅዱ የኢትዮጵያ መንግሥት ተቃዋሚዎችንና ሕዝብን ሰለማሣተፉ እና ሌሎችም ጥያቄዎች ደረሰውናል።
በእነዚህ ነጥቦች ዙሪያ የአድማጮቻችንን ጥያቄ እንዲመልሱልን ሁለት እንግዶችን ጋብዘናል፡፡
ኢንጂነር ሰሎሞን ገብረሥላሴ በዩናይትድ ስቴትሷ ካሊፎርኒያ ግዛት በመንግሥት ውኃ ልማት ክፍል በምሕንድስና ክፍል ያገለግላሉ። በግድቡ መሠራት ላይ ተቃውሞ ባይኖራቸውም ከተቃዋሚዎች ወገን የሚሠነዘሩ ጥያቄዎችን በመተንተን መልስ ይሰጣሉ።
አቶ ብርሃኑ ዳምጤ ደግሞ በኦሃዮ ግዛት የኢትዮጵያ ሲቪሊቲ ፎረም የተወሰነ የውይይት መድረክ የሚያስተናግዱና የኢትዮጵያ መንግሥት ደጋፊዎች አስተባባሪ ናቸው።
ሁለቱ ለአድማጮቻችን ጥያቄዎች የሰጧቸውን መልሶች ያዳምጡ።
(“ስለቁጣው)። አንድ ወጣት እንዲህ ብሎ ፃፈ
“የግብፅ መንግስት ሕዝቡን ረግጦ ለመግዛት የተማመነበት መሳሪያ ከምንም በላይ በሕዝቡ ውስጥ ለረጅም አመታት ያሰረገው የፍርሃት መንፈስ ነው——— ብዙዎች እንደሚናገሩት በግብፅ የተደረገው የቁጣ ቀን (ደይ ኦፍ አንገር)በድህነትና በሥራ አጥነት ምክንያት ወጣቱ የኤኮኖሚ አማራጮችን በማጣቱ አልነበረም ይልቁንስ በሁላችንም ላይ የተጫነው የነፃነትና የክብር እጦት ምክንያት እንጂ ። ግብፃውያን እንደሰው ልጅ መኖር ባለመቻላችን ፣ የስብዓዊ ክብራችን በመዋረዱና የመንግስት ባሮች እንደሆንን በመቆጠራችን ነው “ነበር ያለው። በአትዮጵያ እንደሰሜን አፍሪቃና መካከለኛው ምስራቅ ዓይነት ሕዝባዊ ቁጣ ሊነሳ ይችላል ብለው የሚያምኑት ወገኖች ታድያ የአትዮጵያ ሕዝብ አሁን የደረሰበት ህሊናዊ እውነታ ወይም ሱብጀክቲቭ ኮንዲሽን እንደ ግብፅና ቱኒዚያ (እንደሰው ልጅ መኖር ባለመቻሉ ፣ የስብዓዊ ክብሩ በመዋረዱና እንደ መንግስት ባርያ በመቆጠሩ ምክንያት) ደረጃ ላይ ደርሱዋል ብለው የሚያምኑ ከሆነ “ታላቁ የህዳሴ ግድብ ” በምን አቅሙ ነው ማስቀየሻ ሊሆን የሚችለው?