መለስ ዜናዊ ተቃዋሚዎችን የግብፅ ነጭ ለባሾች ሲል ከሰሰ

(VOA) — መለስ ዜናዊ ትናንት ከፓርላማ አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽ፣ የአንድነት ለፍትሕና ለዴሞክራሲ ፓርቲ አባላት በኢትዮጵያ አመፅ ለመቀስቀስ እየተንቀሳቀሱ በመሆናቸው፥ ድርጊቱ አባላቱን ዋጋ ያስከፍላቸዋል ሲሉ ማስጠንቀቃቸው ይታወቃል።

አንድነት ይህን ከባድ ክስ እንዴት ያየዋል?

የፓርቲውን የውጭ ጉዳይ ኃላፊ አቶ ስዬ አብርሃን አነጋግረናል። ሰሎሞን ክፍሌ ነው ለምሽቱ ዓብይ ርዕስ ያወያያቸው።

ከታሰሩት የመድረክ አባላት አብዛኞቹ የኦነግ አባላት ሽብርና አመፅ ለማቀናጀት ሲንቀሳቀሱ ማስረጃ የተገኘባቸው መሆናቸውንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል። አቶ መለስ በመድረክ በተለይም አባሉ በሆነው በአንድነት ፓርቲ ላይ ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትላንቱ የፓርላማ ንግግራቸው ላይ «ተቃውሞና ሽብር ለመቀስቀስ እየተቀፈቀፈ ነው ያሉት ሤራ» ምን ሊያስከትል እንደሚችል በዝርዝር አላብራሩም። Facebook በሚባለው ማህበራዊ መረጃ መለዋወጪያ መረብ ዌብሳይት የተያዘው ዘመቻ ግን የአቶ መለስ ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ግንባር ሥልጣን የያዘበት 20ኛ ዓመት በመጪው ወር ሲከበር ከፍተኛ ሕዝባዊ ተቃውሞ እንዲደረግ ጥሪ ያቀርባል።

አቶ መለስ በትላንትናው የፓርላማ ንግግራቸው ላይ ተቃዋሚዎችን ብቻ ሳይሆን  በኢትዮጵያ አለመረጋጋት ለመፍጠር ይሞክራሉ ያሏቸውን ሁለት ያካባቢውን ሀገሮችም ከሰዋል። የኦሮሞ ነፃ አውጪ ግንባርን ትረዳለች ያሏትን ኤርትራን እርሣቸውም ፕሬዘዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂን ለመገልበጥ የሚታገሉትን አማጽያን በማገዝ እንደሚበቀሉ አስገንዝበዋል።

በአባይ ወንዝ ላይ ግዙፍ ግድብ ለማነጽ የተያዘውን ጥረት በገንዘብ እንዳይታገዝ ለማገድ ግብፅ ይዛለች ያሉት ዘመቻ እንደማያስፈራቸው ግን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስረድተው፥ ግብጽ ብትተናኰልና፥ አንድም ዓለምአቀፍ ለጋሽ አገር ገንዘብ ለመስጠት ባይስማማም፥ 4 ነጥብ 8 ቢሊዮን ዶላር የሚያስወጣው የሃይድሮ ኤሌክትሪክ ፕሮዤ ሥራ ይቀጥላል ሲሉ አስታውቀዋል።

ዘገባውን ያዳምጡ

3 Comments on “መለስ ዜናዊ ተቃዋሚዎችን የግብፅ ነጭ ለባሾች ሲል ከሰሰ”

  1. Meles is trying to steal the money pretending he is going to build the dam, because he knows before the dam is finished he will be gone with some of the money if not with half of it. We need to think ahead brothers and sisters, all weyane does is playing games ahead of his fears. We should do the same, we should not see things as is, it is not like black and white when it comes to weyane’s state of mind, there are always gray colors, always, cus their mind is tuned to panic and intemidate Ethiopians.

  2. አቶ መለስ አሁን ግድብ መስራት አሁን ጦርነት ማድረግ ምን ስላስጨነቃቸው ነው ለምን ከአመት በፊት አላሰቡበትም ያው የአረቡ ዐለም ጎርፍ ስለመጣባቸው ነው ወይ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

*