የኃይሉ ሻውል ወደ መኢአድ መሪነት መመለስ

የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት መኢአድ ቅዳሜ እና ዕሁድ ባካሄደው ጠቅላላ ጉባኤ ከፖለቲካው ዓለም ራሳቸውን እንዳገለሉ የተናገሩትን የድርጅቱን ፕሬዝዳንት ኢንጅነር ኃይሉ ሻውልን በድጋሚ ለሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት ድርጅቱን እንዲመሩ መርጧል ።

ኃይሉ ሻውል ይህን የፓርቲውን ከፍተኛ ሥልጣን ለሌላ ያስረክባሉ ተብሎ ሲጠበቅ ነበር ። ጠቅላላ ጉባኤው ከዚህ ሌላ ከአንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ ጋር መኢአድ ለመዋሀድ የጀመረው ድርድር ተግባራዊ እንዲሆንም በሙሉ ድምፅ ወመሰኑን የአዲስ አበባው የጀርምን ድምጽ ራዲዮ ወኪል ታደሰ ዕንግዳው ዘግቧል።

ያዳምጡ