የጀርመን የአቶም ሐይል ማዕከላት የስራ ጊዜ መራዘም ያስነሳው ውዝግብ

የጀርመን ጥምር መንግስት ፣ በሀገሪቱ የሚገኙትን የኒዩክልየር ኃይል ማመንጫ ማዕከላት ለመዝጋት ከዚህ ቀደም የተቀመጠውን የጊዜ ገደብ ለመራዘም በቅርቡ የደረሰበት ስምምነት እያወዛገበ ነው ።