የዋጋ ንረት በኢትዮጵያ

ባለፈው ሳምንት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የኢትዮጵያ ብር የምንዛሬ ዋጋ መቀነሱን ካሳወቀ ወዲህ የሸቀጦች ዋጋ ንሯል ።

ታደሰ ዕንግዳው ከአዲስ አበባ እንደዘገበው በአዲሱ የምንዛሪ ተመን ምክንያት የጨመረው ከውጭ ሀገር በውጭ ምንዛሪ ተገዝተው የሚገቡ ዕቃዎች ዋጋ ብቻ ሳይሆን የሀገር ውስጥ ምርቶችም ዋጋ ነው ። የብር የምንዛሪ ተመን በሀያ ሁለት በመቶ ከቀነሰ ወዲህ በኢትዮጵያ ገበያ ላይ መደናገርንም ፈጥሯል ።

ያድምጡ