ክፍት የሥራ ቦታ ማስታወቂያ

መለስና ጉዋደኞቹ ሁለገብ የንግድ ሥራ አክሲዮን ማኅበር በሥሩ ላቓቓማቸው እህት ኩባንያዎች ከ1967ዓ.ም ጀምሮ ላለፉት 36 ዓመታት ለልዩ ልዩ ክፍት የሥራ መደቦቹ ሥራ ፈላጊዎችን እያወዳደረ ሲቀጥር መቆየቱ ይታወቃል፡፡ በ1967ዓ.ም በዐዋጅ ቁጥር ዜአ/666/6606/66ዓ.ም መሠረት በሰባት አባላትና በሰባት ሶቪየት ሠራሽ አሮጌ ክላሽኖች መነሻ ካፒታል ትግራይ ላይ የተቓቓመው መለስና ጉዋደኞቹ ሁለገብ የንግድ ሥራ አክሲዮን ማኅበር በአሁኑ ወቅት በሚሊዮን የሚቆጠሩ አባላትን ያቀፈ ሲሆን ካፒታሉም በብዙ ቢሊዮኖች የሚገመት ዶላር፣ ፓውንድና ዩሮ የደረሰ መሆኑን በማስታወስ በተለይ ደንበኞቹንና ወዳጆቹን እንኩዋን ይህን ያልታሰበ ድንቅ አጋጣሚ ለመታዘብ በቃችሁ በማለት የተሰማውን ጥልቅ ደስታ ይገልጻል፡፡ በዚህ አጋጣሚ ታሪካዊ ጠላቶቹ እንደተለመደው ሁሉ እርር ድብን እንዲሉ ልባዊ ግብዣውን ሲያስተላልፍላቸው አሁንም በታላቅ አክብሮትና ሥጋዊ ሃሤት በመታጀብ ነው፡፡

በዚህ አንጋፋና ስመጥር አክሲዮን ማኅበር ሥር ከታቀፉ እህት ኩባንያዎች መካክል ደደቢት ትምህርትና የትምህርት መሣሪዎች አቅርቦት ሞኖፖሊ ኃ/የተ/የገል ማኅበር አንዱ ነው፡፡ በዚህ እህት ኩባንያ ሥር ደግሞ ደደቢት የውሸት ማሠልጠኛ ዩኒቨርስቲ በመባል የሚታወቅ የትምህርት ተkም ተመሥርቶ ጎን ለጎን ጉልህ እንቅስቃሴውን መጀመሩ አይዘነጋም፡፡

ስለዚህ ይህ ዓለማቀፍ ዝናን ያተረፈው ዩኒቨርስቲ ቀጥሎ ባወጣው አስቸኩዋይ ክፍት የሥራ ቦታ ተወዳድራችሁ መቀጠር የምትፈልጉ ዜጎች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመንና በሪፖርተር ጋዜጣ በታተመ በአሥር ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ አስፈላጊውን የትምህርትና የሥራ ልምድ ማስረጃዎቻችሁን ዋናና ፎቶ ኮፒ ከማመልከቻችሁ ጋር በማያያዝ በኩባንያው የሰው ኃይል ማደራጃና ማስተባበሪያ ዋና መምሪያ ድረስ በአካል በመቅረብ ወይም ለዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከልና ለኢሕአዴግ ጽ/ቤቶች በሁነኛ ሰው በመላክ ማመልከት የምትችሉ መሆናችሁን እንገልጻለን፡፡

የሥራ መደቡ መጠሪያ፤ ምክትል ፕሬዝደንት

ተፈላጊ የትምህርት ደረጃ ፤ በፖለቲካል ሣይንስ ቢያንስ ዲፕሎማ ወይም የመጀመሪያ ዲግሪ ያለውና ለ36 ዓመታት ያህል ሳይታክት ሲዋሽ የዘለቀ ወይም

ለተጠቀሰው የትምህርት ዘርፍ ሠርቲፊከት ያለው ሆኖ ለ18 ዓመታት የመዋሸት ልምድ ያለው ወይም

ከአካባቢ ዕድሮችና ጎረቤቶች እንዲሁም ቤተሰቦችና የቅርብ ሰዎች ለውሸታምነቱ በቂ የጽሑፍ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል

የፒኮሎ ማኪያቬሊን ‹ዘ ፕሪንስ› የሚል መጽሐፍ ቢያንስ ለሰባት ጊዜ ያነበበና ተመሳሳይ ይዘት ያላቸውን መጻሕፍት በንባብ የዳሰሰ

ሰማይን ምድር፣ ምድርን ሰማይ ብሎ በቀላሉ ማሳመን የሚችል ወጥ አቓምና ሃይማኖት የሌለው

ለዋናው ፕሬዝደንት የሚኖረው ታዛዥነት ፍጹማዊ የሆነ ለሌሎች መምህራን “The Global Dynamics of Lying and its Application in Sustaining Power” የሚለውን ኮርስ መስጠት የሚችል ለመሆኑ ከታወቀ የውሸት ማሠልጠኛ ተkም ማስረጃ ማቅረብ የሚችል

ደመወዝ፤ በሚቀርብ የትምህርትና የሥራ ልምድ የሚወሰን ሆኖ ልዩ ልዩ ጥቅማ ጥቅሞችን ሳይጨምር በወር ከብር 110,000.00 እስከ 360,000+

የሥራ ቦታ፤ በቓሚነት አዲስ አበባ እንዳስፈላጊነቱ ግን በተለይ ትግራይ በጣም በተለይ ደደቢትና እጅግ በጣም በተለይ ደግሞ አድዋ ለመስክ ሥራ መመላለስ ይኖራል

ብዛትና ፆታ፤ አንድና ቢቻል ወንድ (አለዚያ ሴትም ብትሆኝ አመልክቺና ዕድልሽን ሞክሪ)

የቐንቐ ችሎታና የትውልድ ሐረግ፤ የኤርትራና የአድዋ ዝርያ ያለውና ትግርኛ መናገር የሚችል አማርኛንና ኦሮምኛን መቻል ተጨማሪ ጠቀሜታ አለው

ለተጨማሪ ማብራሪያ፤ [email protected]