የቱኒዙ ትዕይንት አይናችንን ይገለጥልን ይሆን ?

ማን ነው ያላረረ ማነው ያልተከነ ?

በሀገሩ ጉዳይ ይልተብከነከነ ?

እህህህ… አሃሃሃ.. እያለ ?

በምሬቱ ዜማ ያልተብጠለጠለ ?

 

          መቼም ነገርን ከስሩ ውሃን ከጥሩ እንደሚባል ስለሀገራቸን ጉዳይ ስናነሣ የት ነበርን አሁንስ ወዴት እየሄድን ነው ብሎ መጠየቅ የማንኛውም ዜጋ ግዴታ ነው ብዬ አምናለኡሁ። ታዲያ ይህን አይነት ጥያቄ ጠይቆ መልሱን መረዳት ሲጀምር አይ አበሳቸን ፤ ምነው እግዚአብሄር አልታረቃቸሁ አለን እያልን አይናችንን ወደላይ አንጋጠን እባክህ አምላኬ እትዮጲያን ታደጋት ማለት አይቀሬ ነው። እንደኔ መረዳት በውስጥም በውጭም ያለው እትዮጲያዊ ንጹህ እንቅልፍ መተኛት ካቆመ ዘመናት ተቆጥሮል።

 

         እናቶቻቸንና አባቶቻቸን ልጅ አዋቂውም ስይቀር  በየ አብያተክርስቲያናት እየዞሩ ስለት መሳልና አምላካችውን መማጸን የማያቋርጥ ሥራቸው አድርገውታል።ሕዝብ በሀገሩ ጉዳይ ነዶና ከስሎ በቅርቡ በቱኒዝ እንደሆነው ትእይንት ባዳባባይ እራሱን አቃጥሎ አይሙት እንጂ በየቤቱ ጎዳ ተብከንክኖና ተብስልስሎ ነዶና ጨሶ ህይወቱም ያላፈ ስው አውቃለሁ።  

       

        አይ አምላኬ ምነው አበሳቸንን ባታበዝው ግዞታቸንን ብትገታው እያልን መማጸናቸንን ግን አሁንም ቀጥለናል። “የጨነቀው እርጉዘ የባስበት እመጫት” ምን ያረጋለ ነበር ያለው ያገሬ ስው? በመሆኑም የማናነሥውና የማንጥለው ነገር የለም። ከጭንቀታቸንና ብሦታቸንም የተነሳ  ስለሀገር በምንወያይባቸው “የፓልቶክ” ክፍሎቸ ሁሉ እርስ በእርስ ተከባብረንና ተግባብተን መፍትሄ ለማምጣት በጋራ ከመስራት ይልቅ እርስ በእርስ መዘራጠጥና መዘላለፍን መርጠናል፤ አዲስ ሃሳብ ይዞ የመጣ ስው ካለ ዋናውን ወያኔ አገርቤት እስቀምጠን ሃሳቡን ይዞ የመጣውን  ግለስብ መቸ አጣሁህና አንተ ወያኔ ! እንለዋለን፤ “የወያኔ ቅጥረኞቸ መኖራቸወን ባንዘነጋም”

 

       የፖሎቲካ ድርጀቶቸም ባላቸው ልምድና ተመክሮ በተረጋጋ መንፈስ ብሶተኛውን ዜጋችንን አረጋግቶና አስተባብሮ አቻቸሎና  በሀገር ፍቅር ስሜት ተዋዶና ተሳስሮ በዋናው የሃገር አፍራሹ ወያኔ ላይ እንዲያነጣጥር ከማድረግ ይልቅ የአርባ አመት የሰቆቃ ታሪክ እየተነሳ እናንተ እንዲህ ብታደርጉ ኖሮ እንዲያ አይሆንም ነበር እየተባባልን መዘላለፍ ቀጥለናል። “በፓልቶክ ክፍሎቸ” መሰዳደብና የተለያየ ስም መለጠፍ፤ አንዱ በስጠው የግል አመለካከትና አስተያየት የተዛባ ግንዛቤ እየተወስደ በፓልቶክ ጀነራሎችና የ እለቱ ተረኛ ጠባቂ መኮንኖቸ ከክፍል መባረር የተለመደ ሆኗል። እንዲሀ ያለው የጦርነት ስልት በጠላት ላይ ቢሆነ ምንኛ ውጤታማ የደርገን ነበር ብዬ የፓልቶክ ጀነራሎቸንና መኮንኖቸን ያደነቅኩበት ግዜ እንዳለም ሳልሸሽግ መግለጽ እፈልጋለሁ።

 

            ዜጎቸም ተለማምደውት የሃገራችው ጉዳይ  አላስቀምጥ ብሏችው ይሁን “ፓልቶክ” ሱስ ሆኖባቸው ተባረው መቅረት ስለማይሹ ሌላ ስም ቀይረው “ጀግናው፣ ተብሎ ይጠራ የነበረው ከፋኝ” ብሎ ተቀጥያ ስሙን ቀይሮ በመግባት ሃሳብ መስጠቱን አቁሞ በመስማት ብቻ ተሳታፊ ይሆናል። ድንገትም የማይስማማበትና ትክክል ያልሆነ አስተያየት ሲስማ በጽሁፍ ሃስቡን መግለጽ ሲጀምር ደፈጣ በያዙት “የፓልቶክ ወታደሮቸ” ሳያሰበው በተተኮስ ጥይት ተመትቶ እራሱን ከክፍል ውጪ ያገኘውና ተክኖና ደብኖ ሲጋራ የሚያጨስው ሲጋራውን ይለኩሳል የሚጠጣውም ፍሪጁን ከፍቶ ቢራውን ይጎነጫል የጠነከረውን የለመደም አልኮሉን በብርጭቆ ለመቅዳት እንኳ ንዴቱ ፋታ አልሰጥህ ብሎት ከነጠርሙሱ ያንደቀድቀዋል በምንም ሱስ ያልተያዘውም በረጅሙ ተንፈሶ አይ እግዚአብሔር ማን ይረዳኛ ? ብሎ ማዘኑና መጮሁ የማይቀር ነው።

 

እንግዲህ እስቲ ይታያችሁ እራሳችሁን በሌላው ወገናችሁ ጫማ አርጉና በተርዳችሁት መጠን የግላችሁን ሰዕላዊ መግለጫ ለመስጠት ሞክሩ፣ እኔ የኔን ስጥቻላሁ።

 

ወንድሞቸና እህቶቼ ይህን ሁሉ መዘርዘሬ ስለሀገራችን ጉዳይ ምን ማድረግ ይገባናል ወደሚለው የግል መረዳቴ እንዲወስደን መንደርደሪያም እንዲሆነን ይረዳናል ከሚል ንጽህ ኢትዬጵያዊ ስሜት ተነሥቼ እንጂ የማንንም ኢትዮጵያዊ ወገኔን ስሜት ለመንካት ብዬ እንዳልሆነ ግን እንድትረዱለኝ አደራ እላለሁ። እያንዳንዱም ዜጋ እውነተኛ  በሆነው ኢትዮፒያዊ ስሜት ፈንቅሎት ለሚያደርገው “የፓልቶክ” ተሳትፎም በየክፍሉ እየገቡ ከሚበጠብጡት ወያኔዎቸ በቀር ትልቅ ክበር እንዳለኘ በዚህ አጋጣሚ ልገልጽ እወዳለሁ።

 

        ወገኖቼ፦ዋናው አፍራሹና አገር ገንጣዩ እራሱን (የትግራይ ነፃ አውጪ) ብሎ በመስየም አገርና ህዝብን ከሚያስጨንቀው ወያኔ በቀር ከራሳቸን ወንድሞቸና እህቶቸ ጋራ በአመለካከትና ግንዛቤ አወሳስድ ደረጃ ባንግባባም እንኳን መቻቻል አቅቶን በፓልቶክ የውይይት መደረክ እየጥጨካከንን ከመወያያ ክፍል በማበረርና የማይገቡ የስድብ ውርጅብኞችን ማጉረፉ በውንድሞቻቸንና እህቶቻቸን ላይ ሊፈጥረ የሚቸለውን የስነልቦና ቸግር ከላይ በምእናቤ ስዬ ልገልጽ እንደሞከርኩት ነው።

 

       እኔ እንደሚገባኘ ውይይት ለአንዱ ወይም ለበርካታ ቡድኖች በሚስማማ ሁኔታ ብቻ ቀርቦ አያውቅም፤ መቅረብም የለበትም። ውይይት አንዱ ያላየውን እንዲያይ፤ ያልተረዳውን እንዲረዳ፤ አንዱም ከሌላው እንዲማረና በመጨረሻም የወገኖቸ ሃሳብ ተጨምቆ ወደ አንድ ውጤት ላይ በመደረስ እርምጃ ለመውስድ የሚያዘጋጅ ነው። የሃያ አመት ውይይታቸን ግን እንኳን ወደ እርመጃ ሊያደርስን ቀርቶ ጠላታችንን ለይተን  ሲወርድ ሲዋረድ በመጣው በአንዱና ወሳኝ በሆነው እትዮጵያዊነት ሥም እጅ ለእጅ ተያይዘን በኢትዮጲያዊ ጀግንነት ሊያቆመን አልቻለም።

 

ታዲያ ምን እናደርግ? ፦

 

         እኔ እንደሚገባኝ እኛ ኢትዮጵያዊያኖቸ ጀግኖቸና ሃይማኖታችንን ጠብቅን እስላሙም ክረስቲያኑም አብረን በልተን አብረን ጠጥተን፤ ተከባብረንና እንደየ እምነታቸንም አምላካቸንን ፈርትንና አክብረን የምንኖር ሕዝብ ነን። በመሆኑም ዛሬ የሃገራቸን ቅጥር መፈረስና የህዝብ የስደት ፍልሰትና ጉስቁልና  ህፃናትን በአለም ደርጃ ምእራባዊያኖቸ አማርጠው እንደሽቅጥ ጭነው የሚሄዱበት አገር ኢትዮጵያ መሆኗን እንረዳ።

 

ወላጆቸ ኑሮን መቋቋምና የወለዱትን ልጅ ማሳደግ የማይቸሉበት ደረጃ ላይ በመድረሳቸው፤ እይናችን እያየ ልጃችን ከሚሞት፤  ወይም ከምትሞት እያሉ ልባቸው እያነባ፤ የወለዱትን ልጅ በጉዲፈቻ መልክ በመስጠት ላይ ናቸው።  ይህ ተግባራቸውም ምን ያህል ህሊናቸውን እንደሚያደማው ግንዛቤ ላይ እንደደረስንና ጉስቁልናችው የኛም ጉስቁለና መሆኑን አበክረን ተረድተን ግፉ በቃኘ፤ በማለት ካባቷቻቸን የውረስነውን ኢትዮጲያዊ ቁጣ የምንቆጣበት ደርጃ ላይ እንድረስ።

 

       ዛሬ እኛ በመላው  አለም በስደት ፤ ተበትነንና  በተስጠን ጥገኝነት መኖር መቻላቸን ነፃነትን እንድመጎናጸፍ ቆጥረን  ከሆነ በታሪክ ላይ የምንፈጽመው ታላቅ ስህተትና ድክመት ነው። ስለዚሀም ግዜያዊ  ምቾት ሳይደልለን ድንበር ሳያገደን ወስን ሳይለየን ለነፃነታቸን በአንድነትና በህብረት በመቆም  ታሪካዊ ግዴታችንን መፍጸም እንዳለብን በአንክሮ እንረዳ ።

 

        የጀግኖች አባቶቻችን ታሪክ የሚያስተመርን፤ ለነፃነት ልዩነታቸንን አቻቸለን እጅ ለእጅ ተያይዞ መቆምን ነው። ቅዱሳን መጻሃፍትም የሚያስተመሩን ይህንኑ ነው። ለመጥቀስ ያክል በመጸሃፍ ንህምያ (ምእራፍ 2: ከቁጥር 12 – 20)  ብናነብ የምንረዳው ይሀንኑ እውነታ ነው። እየሩሳሌም ቅጥሮቿዋ መፍረሳቸውን የተረዳው ንህምያ “የስማይ አምላክ ያከናውንልናል እኛም ባሪያዎቹ ተነሥተን እንሠራለን እንዳለ፡” ዛሬ አኛ ኢትዮጵያዊያኖቸ በስደትም ሆነ በሀገር ውስጥ በፖሎቲካ ድርጅት መሰባሰብ ባንቸል እንኳን፤ ይህ የደረስንበት የሃገር ውድቀት ደረጃ የህዝብ በደለና ፍልሰት፤ ስቃይና መከራ ግድ ሊለንና ለነፃነታቸን እጅ ለእጅ ተያይዘን በመቆም ይህን የግፍ አገዛዝም በቃን እንበል። ጊዜውም አሁን እንደሆነ ተረድትን ቆርጠን እንነሳ። የፖሎቲካም ሆነ የአመለካከት ልዩነት ለኢትዮጲያዊነት እንደነት እንቅፋት ምክነያት አደርገን አናቅርብ። አንድነታቸንም ሃይላችንና የነፃነት ምዕራፍ ቀዳጅ  ቁልፍ እንደሆነ አበከረን እነረዳ ።

 

ነፃነትን ለመጎናጸፍ ንቅናቄ እንጅምር፦

 

*    በውስጥም በውጪም የሚገኙ የፖሎቲካ ድረጅቶቸ ከመቼውም በተለየ ሁኔታ በኢትዮፒያ ነፃነት እንደሌለ በማስረገጥ መነሳት ነው። “በወያኔዎች አገላለጽ የነፃነት ትርጉም እንዲህ ነው።  የዲሞክራሲ ስረአት ማለት ስሙን ብቻ ጠርቶ ታፍኖ በጠመንጃ ሃይል መኖር ነው።” እውነተኛው የነፃነትን ትርጉሙን ግን ህዝብ ያውቀዋል።  

 

*    በመሆኑም ገዢውን ሃይል ለማሸንፍ መቻቻልን አጎልብተን ባለም አቀፍ ደርጃ ኢትዮፒያዊያን ሁሉ ምንም ነገር ሣያግዳቸው “እንደክተት ጥሪ” ለነፃነት ምላሽ ሊስጡ የሚችሉበት የተቀናጁ አስራሮቸ ላይ ትኩረት በመስጠት ወትሮ ከተሰራባቸው እቅዶቸና ስልቶቸ በተለየ መንገድ “ነፃነት ለኢትዮጵያ” በሚል ስም አሮጊቱም ሽማግሌውም ወጣቱም ጎልማሳውም ለመስራት እንዲተባበሩ ማስተባበር።

 

*    ዘመኑ በሚፈቅደው ማንኛውም ቴክኖሎጂ በመጠቀም ኢትዮፒያዊ ሁሉ ይሄ የከሌ ሥራ ነው እኔን አይመለከትም ከሚል አስተሳስብ ወጥተን ለነጻነቴ ድርሻዬን ማበርከት አልብኘ በሚል ንጽህ ኢትዮጵያዊ ስሜት ድርሻውን በማበርከት የነፃነት ትግልን ማፋፋም ዋነኛው ተግባራችን ይሁን።

 

*    ለነፃነት መታገል ሚስጥር አይደለምና ባገኘነው አጋጣሚ ሁሉ የወያኔን እኩይ ተግባር በማጋለጥ፤ ለአለም መንግስታትም፣ ለስው ልጅች መብት አስከባሪ ተቋማት ሁሉ በማስታወቅና  በአለም አቀፍ ደርጃ በማስተባበር እንቅስቃሴዎችን በኢትዮጲያዊ መንፈስና ስሜት ነፃነታችንን እስክናገኝ እንታገል።

 

*    የስነጥበብ ስዎቸ፤ ስለነጻነት ይዘምሩ፤ ገጣሚዎቸ ይግጠሙ፤ ፎካሪዎች የጀግነነት ፉከራ ይፎክሩ፤ ስአሊያን በእሰር የሚሰቃየውን እየሳሉ ለአለም ህብረተስብ ያሳውቁ።  የህዝብ መገናኛዎች እስከዛሬ ከተደርገው በላይ ባለሞያዎቸን በማሰማራት በፈጹም እትዮጲያዊ ስሜት የነፃነትን ትግል ያቀጣጥሉ።

*    ሕዝብ የሃገር ሃብት ነውና የተማራውም ያልተማረውም በአስተዳደሩ ምሬት ምክነያት አገር እየለቀቀ እየወጣ እንደሆነ አወቀንና ተገንዝበን፤ እዛው አገሩ ወስጥ እንዲታገሉ ሽንፈትን አሜን ብለው እንዳይቀበሉ ማድረግ አለብን። የቻልን አገር ውስጥ በመግባት እኛም ከጎናቸሁ ነን እንበላቸው። የስደት ኑሮ መፍትሄ እንደማይሆን ካለን ልምድ እናስተምራቸው። በሚያስፈልገው ሁሉ እርዳታን በማድረግ የፖሎቲካ ድርጅቶችንም በማበረታታት በአዲስ መልክ ለኢትዮጲያ ነፃነት በህብረት እንቁም።

 

*    ነፃነት ፈላጊ ነፃነቱን እሥኪቀበል አይተኛምና፤ በታሪክም ትግል ተጀምሮ ድል ሳይቀዳጅ አይቆምምና ፤ትግላቸን ለነፃነት እንደሆነ ተረድተን ድል እስክንቀዳጅ  በመታገል ሀገራችንን ከወራሪው የትግራይ ነፃ አውጪው ወያኔ እናላቃት።  ህዝብን እያፈነና አገርን ለባዕዳን እየሽጠና እያስፈር፤ በአገርና በህዝብ ሉአላዊነት እየቀለደ፤ እትዮጲያዊነትን እያዳከመ በሀገርና በህዝብ ላይ የቀለደውን ወያኔ ከትከሻችን ላይ በአፋጣኘ አራግፈን እንጣል።  

 

*     ያ የአባቶቻችን የጀግንነት መንፈስ በተጸናወተው ኢትዮፒያዊ ጀግንነት ስም በአንድነት ለነፃነት ከታገለን ፤ የነፃነት ጮራ ሳይወል ሳያድር ይፈነጥቃል። በውስጥም በውጭም የምንገኘ  እትዮጲያዊያኖቸም ነፃነታቸንን እንቀዳጃለን። እንደንቦሳም እንዘላለን ምድሪቷም በስላምና በደስታ ትሞላለቸ። ባለም ዙሪያም የተበታተኑት የኢትዮጲያ ልጆቸ ወደምድራቸው ይመለሳሉ ተባብረውም ስላምና ዲሞክራሲን ያስፍናሉ፤ በየሞያቸው ተሰማርተውም አገር ያለማሉ፤ ያቺ አባቶቻቸን ደማቸውን አፍስስው አጥንታቸውን ከስክስው ያቆዮት ኢትዮጵያ እንደገና ወደቦታዋ ትመለሳለቸ  በተድላና በደስታም እንኖራለን።

 

 

 

እግዚአብሄር ተግባራዊ እንድናደርግ ማስተዋሉን ያብዛልን አሜን !!

 

ሎሚ ተራ ተራ ነኘ በቸር  ይግጠመን !

[email protected]