የዑጋዴን ብሔራዊ ነፃ አውጪ ግንባር የኢትዮጵያ መንግሥት በርካታ ሲቪሊያንን ገደለ ሲል ከሰሰ

(ኢትዮ እማማ)
የዑጋዴን ብሔራዊ ነፃ አውጪ ግንባር Ogaden National Liberation Front (ONLF) የኢትዮጵያ መንግሥት በርካታ ሲቪሊያንን ገደለ ሲል ከሰሰ።

የግንባሩ ወኪል ሐሰን መሐመድ ኑር ሙቃዲሾ ለሚገኘው ለሸበሌ ሬዲዮ ዛሬ በሰጡት መግለጫ የኢትዮጵያ መንግሥት ወታደሮች በርካታ ሱማሊያን በሚገኙበት በምስራቅ ኢትዮጵያ በከፈተው ጥቃት ምንም ግንኙነት የሌላቸውን 20 ሲቪላውያንን ጨፍጭፏል በማለት ለሬዲዮው ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ መንግሥት ወታደሮች በርካታ ጊዚያት በሲቪላውያን ላይ ወታደራዊ ጥቃት እንደሚፈፅምና የሰባዊ ገፈፋም በተለያየ ወቅት በአካባቢው እንደሚያካሂድ ተናግረዋል። በተለይም በቆራሄ ፣በደጋህቡርና በፋርማዶ በመሳሰሉ አብዛኛው ሱማሊያን በሚኖሩብት አካባቢ ላይ የሠባዊ ረገጣና በሱማሊያን ላይ ግድያዎች የፈፅማል በማለት የኢትዮጵያ መንግሥትን ይከሳሉ።የዑጋዴን ብሔራዊ ነፃ አውጪ ግንባርOgaden National Liberation Front (ONLF) ላቀረበው ክስ ከኢትዮጵያ መንግሥት የተሰጠ ምላሽ የለም።