የደርግ ባለስልጣናት በያዝነው ወር የፈታሉ

ኢትዮ እማማ
በኢትዮጵያ የሚገኙ 4ቱ የሀይማኖት መሪዎች በማረሚያ ቤት ያሉ የቀድሞ የደርግ ባለስልጣናት ከእስር ይፈቱ ዘንድ ይቅርታ እንዲደረግላቸው የኢትዮጵያ መንግስትንና ህዝብን ይቅርታ እንዲያደርጉላቸው ጠየቁ።ባለስልጣናቱ በያዝነው ወር የፈታሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ትናትና በኢንተርኮንትኔታል ሆቴል በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ የጠየቁት የአትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ፤የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት፤የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስትያንና የኢትዮጵያ መካነ ኢየሱስ ቤተክርስትያን የሀይማኖት አባቶች ናቸው።እነዚህው የሀይማኖት አባቶች ይቅርታውን ለመጠየቅ የተነሳሱት በማረሚያ ቤት የሚገኙት የደርግ ባለስልጣናት የሀገሪቱ መንግስትና ህዝቡ ይቅርታ እንዲያደረግላቸው በጠየቁት መሰረት ነው ተብሏል። ባለፉት 2 አመታትም እነዚሁ የሀይማኖት መሪዎቹ የተለያዩ ስራዎችን ሲያከናወኑ መቆየታቸውንም በጋዜጣዊ መግላጫቸው የገለጹ ሲሆን ማንኛውም ነገር በይቅርታና እርቅ መጨረስ ለሀገሪቱ ሰላምና አንድነት ወሳኝነት ያለው መሆኑን የአትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሊቀ ጳጳስ ብፁእ ወቅዱስ አቡነ ፓውሎስ ተናግረዋል።

የሀይማኖት አባቶቹ በጋዜጣዊ መግላጫቸው ላይ የሀገራችን ባህል የተጣላ ማስታረቅ ፣የበደለም፣ የተበደለም ይቅር መባባል፤ ዋንኛው መለያ መሆኑን ጠቁመው በይቅርታና እርቅ መቃቃር፣ መለያየትና ፀብ እንደሚሸነፍ ተናግረዋል።

የሀይማኖት መሪዎች ከሰማእታት ሀውልት አሰሪ ኮሚቴና ከሰለባዎቹ ቤተሰቦች ጋር ከጥሩ መግባባት ላይ መደረሱን ገልጸዋል።የፊታችን ታህሳስ 16 ቀን ከ500 በላይ ሰዎች በሚገኙበት በዳይና ተበዳይ ፊት ለፊት ተገናኝተው ይቅር እንደሚባባሉና ቀኑም የይቅርታና የሰላም ቀን ተብሎ እንደሚሰየም በተጨማሪም በዚሁ ቀን የደርግ ባለስልጣናቱ ከእስር ሊፈቱ እንደሚችሉ ተጠቁሟል።